Telegram Group & Telegram Channel
#በይረሙን (የዛሬው የዕለተ ዓርብ የተለየ ጾም ጉዳይ)
᯼͞᳀͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͞ ͟͞ ̸ ͟͞  ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᯼᳀᯼͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͟͞ ͟͞ ͟͞ ͟͞ ̸͞͝ ͟͞᳀᯼

✧ "በይረሙን" ምንድር ነው?

መጽሐፈ ስንክሳራችን የጥር ፲ ተዝካር  የጥምቀቱን ዋዜማ መታሰቢያ  ስለ «ጾመ ዕለት ዋሕድ ⇨ ዘስሙ ገሀድ» በቁጥር ፬ ሲገልጥ እንዲህ ብሏል ፦

☞ ወለእመ ኮነ በዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሑድ ይጹሙ በዕለተ አርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት!

☞ በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን [በይረሙን ያለውን አማርኛው «ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው» ብሎ ይፈታውና]  በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ!

☞ And if the day of Bayramum fall on the First Day of the week, or on the Sabbath of the Jews, one shall fast on the Fourth Day of the week [friday] preceding it until the evening!

ታዲያ በዘንድሮው ልክ ስንክሳሩ እንዳስቀመጠው በይረሙኑ ቅዳሜ ስለዋለ ዓርብን ሠዓት ጨምረን መጾም  እንዳለብን ልንረዳ ይገባል።

#በ_ይ_ረ_ሙ_ን

በሰዋስው ሊቅነት በሀገራችን ቀድመው የሚወሱት ኪዳነ ወልድ (በመጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ) እንዲኽ የሚል ፍንጭ ያስቀምጣሉ ለበይረሙን መነሻው አረቢኛው በራይም ሲሆን ትርጉሙ  ቅድሳት፣ ዕለተ ቅድሳት፣ አስተርእዮ ጥምቀት ማለት ነው ብለው እንደ ምንጭ  ስንክ ጥር ፲ን ተመልከት ይላሉ!

      ይኽን ይዞ የውጪውን መዛግብተ ቃላት የሚያካልል ቢኖር ከዚህ መድረስ ይችላል  በትርጉም  በይረሙን ያለው  በረይሙን [Baraymun] የሚለውን ሲሆን የአረቡ ባራሙን baramun በግሪኩም παραμόνη ፓራሞን (ፓራሞኔ)  በሚል አቻ ትርጉም ቃሉ መታወቁ ተገልጧል!
☞ Comparative dictionary of Geʻez (classical Ethiopic) : Geʻez-English / English-Geʻez, with an index of the Semitic roots /. by Wolf Leslau. Page 109

የአፍሪቃ ድንበር፣ መካነ ጻዕር፣ ልሳነ ባህር… የሚሰኙት ግብጣውያኑ የቅብጥ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቃላትን ምንነት [Dictionary of Church Terms] በዘገቡበት ድረ መካን ላይ ፓራሞን (Paramone)
የሚለውን ቃል ከነ ሥርዓተ በዓሉ በተከታዩ መንገድ አብራርተውልናል!

  ↳ A Greek term meaning watch, vigil, especially on the eve of a festival. Its Arabic equivalent, Paramun, is a term generally used for the vigils of the Nativity of Our Lord Jesus Christ and of the Epiphany. It is a fast requiring abstention from eating fish, meat, eggs, milk, butter, and cheese. If the day before the feast happens to be Saturday or Sunday, then the paramone begins on Friday because it is not permitted to fast on Saturday or Sunday.

↷ ፓራሞን የግሪክ ቃል ሲሆን መጋድ (ገሃድ መሆን መታየት መገለጥ) ፣ ዋዜማ ይልቁንም ደግሞ የክብረ በዓሉ ፊተኛው ቀን የሚውል ዕለት ተብሎ ይገለጣል። የአረቢኛው አቻ ቃል ፓራሙንም በአጠቃላይ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደትና በዓለ ጥምቀት ዋዜማ የሚነገር ከዓሣ ከሥጋ ከእንቁላል ከወተት ከቅቤና ከአይብ መከልከልን የሚጠይቅ የጾም ቀን ነው! ታዲያ ክብረ በዓሉ አስቀድሞ የሚውለው ይኽ ዕለት በቀዳሚትና በእሑድ ሰንበታት ላይ ያረፈ እንደሆን ፓራሞኑ የሚጀምረው ዕለተ ዓርብ ይሆናል ምክንያቱም በሰንበታቱ ከጥሉላቱ እንጂ ጨርሶ ከመባልዕት መከልከል አይፈቀድምና!

#የበይረሙን_ጦም?

ስንክሳራችን “ይጹሙ በዕለተ ዓርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት! … በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ" ይላል! ተጨማሪ ሰንበታቱን በሚመለከት ዓርብን ጦመናል ብለን ጥምቀቱ (ጥር ፲፩) እሑድ ሲውል ቅዳሜ  እንዳንበላ ሰኞ ሲውል ደግሞ እሑድ እንዳንበላ «ይትዓቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ…  ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ» ይላል! (ጥሉላት ማለት ቅባታማ ሥጋ ቅቤ ዕንቍላል ወተት የሰባ የድሎት ምግብ…የእንሰሳት ተዋፅኦ የሚለውን ይገልጣል)

በአጭሩ ዘንድሮ በዓሉ የዋለው እሑድ ነው! ስለዚኽ ጦመ «በይረሙን» የሚባለው ቅዳሜን ከጥሉላት መከልከልና ዓርብን ግን እስከ ምሽት ከምግብ መከልከል! (ይኽ ግን   በሌላ ዓመት ደግሞ እንዲኹ በዓሉ ሰኞ ቢውል ቅዳሜን ከምግብ ተከልክሎ መዋል ስለማይገባ  በተመሳሳይ ዓርብን   እነደዚሁ እስከ ምሽት ሳይበሉ መቆየት የሚለውን ይገልጣል!

tg-me.com/orthodox1/13072
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/orthodox1/13072

View MORE
Open in Telegram

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Launched in 2013, Telegram allows users to broadcast messages to a following via “channels”, or create public and private groups that are simple for others to access. Users can also send and receive large data files, including text and zip files, directly via the app.The platform said it has more than 500m active users, and topped 1bn downloads in August, according to data from SensorTower.

The SSE was the first modern stock exchange to open in China, with trading commencing in 1990. It has now grown to become the largest stock exchange in Asia and the third-largest in the world by market capitalization, which stood at RMB 50.6 trillion (US$7.8 trillion) as of September 2021. Stocks (both A-shares and B-shares), bonds, funds, and derivatives are traded on the exchange. The SEE has two trading boards, the Main Board and the Science and Technology Innovation Board, the latter more commonly known as the STAR Market. The Main Board mainly hosts large, well-established Chinese companies and lists both A-shares and B-shares.

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 from tw

Telegram ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
FROM USA